ምርጡ የእርግዝና መከላከያ
💊 የእርግዝና መከላከያ ኪኒን (COC)
የእርግዝና መከላከያ ኪኒን ኤስትሮጅን (Estrogen) እና ፕሮጀስቲን (Progestin) የተባሉ ሁለት ሆርሞኖችን የያዘ መድኃኒት ነው። በዋናነት እንቁላል ከእንቁላል ማስለቀቂያ እንዳይወጣ በማድረግ እርግዝናን ይከላከላል። በትክክል ሲወሰድ እርግዝናን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ውጤታማነት አለው። የወር አበባን ለማስተካከልና ህመሙን ለመቀነስም ሊረዳ ይችላል።
💊 ኪኒኑን እንዴት መውሰድ ይቻላል?
1. መቼ መጀመር ይቻላል? የወር አበባሽ በጀመረ በመጀመሪያዎቹ 5 ቀናት ውስጥ ከጀመርሽ ተጨማሪ የእርግዝና መከላከያ ሳያስፈልግ ጥበቃ ይሰጣል። ከዚያ በኋላ ከጀመርሽ ግን እርግዝና እንደሌለ ማረጋገጥና ለመጀመሪያዎቹ 7 ቀናት ኮንዶም መጠቀም ወይም ወሲባዊ ግንኙነትን መቆጠብ ያስፈልጋል።
2. በየቀኑ አንድ ኪኒን ውሰጂ። በየቀኑ በተመሳሳይ ሰዓት አንድ ኪኒን ውሰጂ። በማሸጊያው ላይ የተጻፈውን መመሪያ ተከተዪ።
3. ቀጣዩን ማሸጊያ በትክክል ጀምሪ።
- 21 ኪኒን ያለው ማሸጊያ፦ 21 ኪኒኖችን ከጨረስሽ በኋላ ለ7 ቀናት ቆይተሽ ቀጣዩን ማሸጊያ ጀምሪ።
- 28 ኪኒን ያለው ማሸጊያ፦ በየቀኑ አንድ ኪኒን ውሰጂ፤ ማሸጊያው ሲያልቅ ሳታቋርጪ ቀጣዩን ጀምሪ።
4. ኪኒን ከረሳሽ ምን ታደርጊያለሽ? መፍትሔው ያመለጡሽ የኪኒን ብዛትና የተረሳበት ጊዜ ላይ ይመረኮዛል። የመድኃኒቱን መመሪያ ተመልከቺ ወይም የጤና ባለሙያን አማክሪ።
⚠️ ኪኒኑን መውሰድ የማይመከርላቸው ሰዎች
ይህ ኪኒን ለሁሉም ሰው ተስማሚ አይደለም። ከሚከተሉት ሁኔታዎች አንዱ ካለብሽ ከመጀመርሽ በፊት የጤና ባለሙያን አማክሪ፦
- ማይግሬን ከኦራ ጋር (Migraine with aura)፦ ለምሳሌ ከራስ ምታት በፊት የብርሃን ብልጭታ ወይም የእይታ ለውጥ ካለ።
- የደም መርጋት ታሪክ፦ ለምሳሌ በእግር ወይም በሳንባ የደም መርጋት ካጋጠመሽ።
- ከፍተኛ የደም ግፊት፣ ስትሮክ ወይም የልብ በሽታ።
- የጡት ካንሰር፦ አሁን የጡት ካንሰር ካለ።
- ከባድ የጉበት በሽታ።
- እድሜሽ 35 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ሆኖ ሲጋራ የምታጨሺ ከሆነ።
ከወለድሽ በኋላ ባለው የተወሰነ ጊዜ፣ በተለይም ጡት ለምታጠቡ እናቶች፣ ይህ ኪኒን ተስማሚ ላይሆን ይችላል። እንዲሁም አንዳንድ የሚጥል በሽታ መድኃኒቶች የኪኒኑን ውጤታማነት ሊቀንሱ ይችላሉ።
❤️ አስፈላጊ ማስታወሻዎች
- ይህ ኪኒን ከኤችአይቪና ከሌሎች በግብረ ሥጋ ግንኙነት ከሚተላለፉ በሽታዎች አይከላከልም። ለዚህ ኮንዶም መጠቀም ያስፈልጋል።
- በመጀመሪያዎቹ ወራት ማቅለሽለሽ፣ ጡት መምታት ወይም ትንሽ የደም መፍሰስ ሊያጋጥም ይችላል።
- የደረት ህመም፣ ድንገተኛ የትንፋሽ ማጠር፣ የአንድ እግር እብጠት ወይም ድንገተኛ የነርቭ ምልክቶች ካጋጠሙሽ አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ፈልጊ።
ሌሎች ምክሮችን Tena Beje አፕልኬሽን ላይ ታገኛለሽ።

