በእርግዝና ጊዜ የተከለከሉ 5 ምግቦች


በእርግዝና ወቅት አንዳንድ ምግቦችና መጠጦች ለእናትና ለልጅ የጤና ችግር ሊያመጡ ስለሚችሉ  መመገብ የለብሽም።

1. በደንብ ያልበሰለ ስጋ፣ እና እንቁላል

ጥሬ ወይም በደንብ ያልበሰለ ስጋ፣ እና እንቁላል ከመመገብ ይቆጠቡ። እነዚህ ምግቦች የምግብ መመረዝን እና ሌሎች ኢንፌክሽኖችን የሚያመጡ ተህዋሲያን ሊይዙ ይችላሉ።

2. ያልፈላ ወተት

ያልፈላ ወተትና ከዚህ የተዘጋጁ የወተት ተዋጽኦዎችን ያስወግዱ። ጎጂ ተህዋሲያን ሊኖራቸው ስለሚችል በእርግዝና ወቅት ኢንፌክሽን ሊያስከትሉ ይችላሉ።

3. ያልታጠቡ ፍራፍሬዎችና አትክልቶች

ፍራፍሬና አትክልት ከመመገብ በፊት በደንብ እጠቡ። ያልታጠቡ ምግቦች ከአፈር ወይም ከተበከሉ ንጣፎች የመጡ ተህዋሲያንን ወይም ባክቴርያ ሊይዙ ይችላሉ።

4. ከመጠን በላይ ቡና

በእርግዝና ወቅት የቡና መጠን መገደብ ይመከራል። በቀን ከ 2 ሲኒ በላይ ቡና እንዳይወስዱ ይጠንቀቁ። 

5. አልኮል

በእርግዝና ወቅት አልኮልን ሙሉ በሙሉ ያስወግዱ። አልኮል ወደ ልጁ በመድረስ የልጁን እድገት ሊጎዳ ይችላል። በእርግዝና ወቅት ምንም ዓይነት የአልኮል መጠጣት የለብሽም።

Popular posts from this blog

በእርግዝና ወቅት አሳሳቢ 10 ምልክቶች