የወር አበባ መዛባት
በህክምናው የወር አበባሽ ተዛብቷል የምንለው እነዚህ 4 ምልክቶች ካሉብሽ ነው። በዝርዝር ነግርሻለው አንቺም like እና copy link እያረክሽ ተመልከቺ።
የመጀመሪያው የሚፈስሽ ደም ብዙ ከሆነ ይህም ማለት የንፅህና መጠበቂያ ሞዴስሽ የምትቀያይሪው በየ3 ሰዓት ልዩነት ከሆነ ወይም የደም ማነስ ምልክት ከታየብሽ ለምሳሌ ራስ ማዞር ፣ ድካም ወይም ጆሮ ላይ የሚጮህ ድምፅ መሰማት።
2ኛው የሚቆየው ከ 8 ቀን በላይ ከሆነ ኖርማል የወር አበባ የሚቆየው ከ 3 እስከ 7 ቀን ነው። በወር አበባ ወቅት ህመም የሚያስቸግርሽ ከሆነ በቤት ውስጥ ማዘጋጀት የምትችዪውን መፍትሄ በሌላ Video ሰርቼልሻለሁ እሱን መመልከት ትችያለሽ።
3ኛው የወር አበባሽ የሚመጣው ከ 21 ቀን በታች ወይም ከ 35 ቀን በላይ ከሆነ
4ኛው በሁለት የወር አበባዎች መካከል ያለው ልዩነት ከ 10 ቀን በላይ ከሆነ ለምሳሌ በዚ ወር በ 22 ቀን መቶ በቀጣይ በ 34 ቀን ከመጣ ልዬነቱ ከ 12 ስለሆነ የወር አበባሽ ተዛብቷል ማለት ነው።
