የደም ማነስ ምልክቶች

በእርግዝና ወቅት የደም ማነስ በተለይ በቂ አይረን (ቀይ መዳኒት) ካልወሰድሽ ሊከሰት ይችላል። ከሚከተሉት ምልክቶች ካሉዎት ምርመራ ማድረግ ይገባል።

  1. ከፍተኛ ድካም – በቂ እረፍት ቢያደርጉም በጣም መድከም።
  2. ማዞር – በተለይ በፍጥነት ሲነሱ ራስ መዞር።
  3. የቆዳ መገርጣት – ከንፈር ወይም የዓይን ውስጥ ክፍል ከመደበኛው ይልቅ መገርጣት።
  4. ትንፋሽ ማጠር – ቀላል እንቅስቃሴም ቢሆን በቀላሉ መተንፈስ መከብድ።
  5. የልብ ምት መፍጠን – ልብ ከመደበኛው በፍጥነት መምታት።

አስፈላጊ: እነዚህ ምልክቶች ብቻቸውን የደም ማነስን አያረጋግጡም። የደም ምርመራ በማድረግ የሂሞግሎቢን መጠን መመርመር ያስፈልጋል።


መፍትሄውን በዝርዝር Tena Beje አፕልኬሽን ላይ ታገኛለሽ። ተመልከቺ

Popular posts from this blog

በእርግዝና ወቅት አሳሳቢ 10 ምልክቶች

በእርግዝና ጊዜ የተከለከሉ 5 ምግቦች