የ 72 ሰዓት መከላከያ የጎንዮሽ ጉዳቶች

የ 72 ሰዓት መከላከያ ያልታሰበ ወይም ድንገተኛ የግብረ ሥጋ ግንኙነት በኋላ እርግዝናን ለመከላከል የሚወሰድ መድሃኒት ነው።

1. የወር አበባ ለውጥ

የወር አበባሽ ከተለመደው ቀድሞ ወይም ዘግይቶ ሊመጣ ይችላል።

2. የሆድ ህመም ወይም ቁርጠት

እንደ የወር አበባ ህመም የሚመስል የሆድ ቁርጠት ሊኖር ይችላል።

3. ትንሽ የደም መፍሰስ

የወር አበባሽ ከመድረሱ በፊት ትንሽ የደም ጠብታ ወይም spotting ሊከሰት ይችላል።

4. ማቅለሽለሽ

ክኒኑን ከወሰዱ በኋላ ማቅለሽለሽ ሊሰማ ይችላል።

5. ራስ ምታት

ቀላል ወይም ጊዜያዊ ራስ ምታት ሊከሰት ይችላል።

6. ድካም

ከክኒኑ በኋላ ለጥቂት ጊዜ የድካም ስሜት ሊኖር ይችላል።

7. ማስታወክ

አንዳንድ ሰዎች ከወሰዱ በኋላ ሊያስታውኩ ይችላሉ። ክኒኑን ከወሰዱ በኋላ በቅርብ ጊዜ ካስታወኩ ተጨማሪ መጠን መውሰድ እንዳለብዎ የጤና ባለሙያ ያማክሩ።

Popular posts from this blog

በእርግዝና ወቅት አሳሳቢ 10 ምልክቶች

በእርግዝና ጊዜ የተከለከሉ 5 ምግቦች