እርጉዞች ማድረግ ያለባቸው 5 ነገሮች
እርጉዝ መሆንሽን ካወቅሽ በኋላ ማድረግ ያለብሽ 5 አስፈላጊ ነገሮች! 🤰
1ኛ — ፎሊክ አሲድ ጀምሪ የፎሊክ አሲድ አጠቃቀም በእርግዝና መጀመሪያ ጊዜ በጣም አስፈላጊ ነው።
2ኛ — እርግዝናው በማህፀን ውስጥ መሆኑን አረጋግጪ በጤና ባለሙያ እና በሚያስፈልግበት ጊዜ በአልትራሳውንድ እርግዝናው በማህፀን ውስጥ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል።
3ኛ — አልኮል እና ሲጋራ አቁሚ እርግዝናን ካወቅሽ በኋላ አልኮልን እና ሲጋራን መጠቀም አቁሚ።
4ኛ — የመጨረሻ የወር አበባሽን ቀን መዝግቢ የመጨረሻ የወር አበባሽ የጀመረበትን ቀን መመዝገብ የእርግዝናሽን ዕድሜ እና የምትገመተውን የመውለጃ ቀን ለመለየት ይረዳል።
5ኛ — ያለ የጤና ባለሙያ ምክር መድሃኒት አትውሰጂ እርጉዝ ከሆንሽ በኋላ ማንኛውንም መድሃኒት ከመውሰድሽ በፊት የጤና ባለሙያን አማክሪ።
ሌሎች ምክሮችን ለማግኘት ወደ Tena Beje application ተመለሺ።
